ምዕራፍ 4
እከክ 10,000 ያሉ ሙሉ ቁጥሮችን መደመር እና መቀነስ
በ 3ኛ ክፍል ሒሳብ ትምህርት በምዕራፍ 4 ላይ ስለ እከክ 10,000 ያሉ ሙሉ ቁጥሮችን መደመር እና መቀነስ እንማራለን
ስለ እከክ 10,000 ያሉ ሙሉ ቁጥሮችን መደመር እና መቀነስ ከተማርን በኃላ ሁላቹም
- እስከ 10000 ያሉ ሙሉ ቁጥሮችን መደመርት ችላላችሁ።
- እስከ 10000 ያሉ ሙሉ ቁጥሮችን መቀነስ ትችላላችሁ።
- መደመር እና መቀነስ ስሌትን በመጠቀም የቃላት ፕሮብሌም መፍታት ትችላላችሁ።
4.1 እስከ 10,000 ያሉሙሉቁጥሮችን መደመር እንድምናአላቹሁ ተማሪዎች
ዛሬ ደግሞ ስለ እስከ 10,000 ያሉ ሙሉ ቁጥሮችን መደመር ልንማማር ተገናኝተናል
ዝግጁ ናቹሁ ልጆች?
ተማሪዎች ባለ ሁለት ሆሄ ሙሉ ቁጥሮችን መደመር የተማራቹትን ታስታውሳላችሁ አይደል?
አሁን ደግሞ የ1000 ብዜቶችን ወይም ሁለት አዎንታ ቁጥሮች ወደ ጎን እና ወደ ቁልቁል መደመር እንማራለን ማለት ነው።
ለምሳሌ1
2000 እና 5000ን እስቲ እንደምር ዝግጁ ናችሁ ? ተማሪዎች ጥያቄን ከመስራታችሁ በፌት ከታች ያለውን ዓረተ ነገር አስተውሉ
ሁለት ከ10,000 የሚያንሱ የ1000 ብዜት ሙሉ ቁጥሮችን በቃል ስትደምሩ በሺ ቤት የሚገኙትን ሆሄዎች ደምራቹ በቀኝ በኩል ሶስት ዜሮችን መጻፍ አለባችሁ።
በዚህ መሰረት ምሳሌ አንድን እንስራ
2000 እና 5000 = ________፟
በ2000 ውስጥ በሺ ቤት የሚገኝ ሆሄ 2 ነው።
በ5000 ውስጥ በሺ ቤት የሚገኝ ሆሄ 5 ነው።
አሁን ደግሞ በሺ ቤት የሚገኙትን ሆሄዎች 2 እና 5 ትን እንደምራለን 2 + 5 = 7
በመቀጠል በቀኝ በኩል ያሉትን ሶስት ዜሮዎች እንጨምራለን ማለት ነው።(በቀስት ያሉትን 0 መደመር(መጨመር)
ስለዚህ 7000 ይሆናል ማለት ነው። ተጨማሪ ምሳሌ እናያለን ምሳሌ ቁጥር 2 6000ን እና 3000
በ6000 ውስጥ በሺ ቤት የሚገኝ ሆሄ 6 ነው።
በ3000 ውስጥ በሺ ቤት የሚገኝ ሆሄ 3 ነው።
በሺ ቤት የሚገኙት ሆሄ ስንድምር 9 በመሆኑ። የ6000 እና 3000 ድምር 9000 ነው።
ተማሪዎች አሁን ደግሞ የመደመር ግድግዳዎች ከመሰረቱ ጀምሮ የ1000 ብዜቶችን እየደመርን ወደ ላይ መውጣት እናያለን።
ዝግጁ ችሁ?
ምሳሌ 1 90900 ተማሪዎች ከላይ ያለውን ምስል ተመለከታችሁ ። ምን አስተዋላችሁ?
ተማሪዎች እስቲ አብረን ከታች ወደ ላይ ሁለት ሁለት ሳጥን አንድ ላይ እንደምር ውጤቱ ከላይ ያለውን አንዱን ሳጥን ይሆናል።(በቀስት 2000 እና 2000 ይሆናል 4000 ማለት ነው።)
ተማሪዎች ቀጥሎ ያለውን ሳጥን እንደምር ምሳሌ ቁጥር 1
2000 እና 3000 ይሆናል 5000
አሁን ደግሞ 4000 እና 5000 ስንደምር ይሆናል 9000 ማለት ነው። ምሳሌ ቁጥር 2 ተማሪዎች ከላይ ያለውን ምስል ተመለከታችሁ ። ምን አስተዋላችሁ?
ተማሪዎች እስቲ አብረን ከታች ወደ ላይ እንደተማራችው ሁለቱን ሳጥን አንድ ላይ ስንደምር ውጤቱ ከላይ ያለውን አንዱን ሳጥን ይሆናል።
3000 እና 1000 ይሆናል 4000 ማለት ነው።
ቀጥሎ ያለውን ሳጥን እንደምር 1000 እና 1000 ይሆናል 2000 በቀስት ማሳየት) አሁን ደግሞ 4000 እና 2000 ይሆናል 6000 ማለት ነው። ተማሪዎች አሁን ደግሞ እስካሁን የተማራቹትን ጥያቄ ልጠይቃችሁ።
1. የሚከተሉትን ቁጥሮች ደምሩ።
ሀ.9000 እና 1000
ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት?በጣም ጥሩ ልጆች!
10,000 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳቹኃል ማለት ነው።
እስቲ አብረን እንስራ ዝግጁ ናችሁ?
ተማሪዎች እንደተማራችሁት በመጀመሪያ የሺ ቤት ሆሄ እንለያለን 9000 ውስጥ የሺ ቤት 9 ነው።
1000 ውስጥ ደግሞ የሺ ቤት 1 ነው።
አሁን ደግሞ ልጆች ሁለቱን የሺ ቤቶች አንድ ላይ እንደምራለን 9 + 1 = 10 ይሆናል ማለት ነው።
በመቀጠል በቀኝ በኩል ያሉትን ሶስት ዜሮዎች እንጨምራለን ማለት ነው። (በቀስት ያሉትን 0 መደመር)
10,000 ይሆናል ማለት ነው። ተማሪዎች ስለዚህ የመለሳቹት መልስ ትክክል ነው ማለት ነው።
ለ.5000 እና 4000
ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት?በጣም ጥሩ ልጆች!
9000 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳቹኃል ማለት ነው።
እስቲ አብረን እንስራ ዝግጁ ናችሁ?
ተማሪዎች እንደተማራችሁት በመጀመሪያ የሺ ቤት ሆሄ እንለያለን 5000 ውስጥ የሺ ቤት 5 ነው።
4000 ውስጥ ደግሞ የሺ ቤት 4 ነው።
አሁን ደግሞ ልጆች ሁለቱን የሺ ቤቶች አንድ ላይ እንደምራለን 5 + 4 = 9 ይሆናል ማለት ነው።
በመቀጠል በቀኝ በኩል ያሉትን ሶስት ዜሮዎች እንጨምራለን ማለት ነው።
9000 ይሆናል ማለት ነው። ተማሪዎች ስለዚህ የመለሳቹት መልስ ትክክል ነው ማለት ነው።
ሐ.2000 እና 2000
ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት?በጣም ጥሩ ልጆች!
4000 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳቹኃል ማለት ነው።
እስቲ አብረን እንስራ ዝግጁ ናችሁ?
ተማሪዎች እንደተማራችሁት በመጀመሪያ የሺ ቤት ሆሄ እንለያለን 2000 ውስጥ የሺ ቤት 2 ነው።
2000 ውስጥ ደግሞ የሺ ቤት 2 ነው።
አሁን ደግሞ ልጆች ሁለቱን የሺ ቤቶች አንድ ላይ እንደምራለን 2 + 2 = 4 ይሆናል ማለት ነው።
በመቀጠል በቀኝ በኩል ያሉትን ሶስት ዜሮዎች እንጨምራለን ማለት ነው። (በቀስት ያሉትን 0 መደመር)
4000 ይሆናል ማለት ነው። ተማሪዎች ስለዚህ የመለሳቹት መልስ ትክክል ነው።
መ.3000 እና 6000
ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት?በጣም ጥሩ ልጆች!
3000 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳቹታል ማለት ነው።
እስቲ አብረን እንስራ ዝግጁ ናችሁ?
ተማሪዎች እንደተማራችሁት በመጀመሪያ የሺ ቤት ሆሄ እንለያለን 3000 ውስጥ የሺ ቤት 3 ነው።
6000 ውስጥ ደግሞ የሺ ቤት 6 ነው።
አሁን ደግሞ ልጆች ሁለቱን የሺ ቤቶች አንድ ላይ እንደምራለን 3 + 6 = 9 ይሆናል ማለት ነው።
በመቀጠል በቀኝ በኩል ያሉትን ሶስት ዜሮዎች እንጨምራለን ማለት ነው።(በቀስት ያሉትን 0 መደመር)
9000 ይሆናል ማለት ነው። ተማሪዎች ስለዚህ የመለሳቹት መልስ ትክክል ነው ማለት ነው።
2.የሚከተሉትን የመደመር ግድግዳዎች በመደመር ክፍት ቦታዎችን ሙሉ።
ሀ. ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት?በጣም ጥሩ ልጆች!
የመጀመሪያ ሳጥን ውሰጥ 3000 ሁለተኛው ሳጥን ወስጥ ደግሞ 7000 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳቹኃል ማለት ነው።
እስቲ አብረን እንስራ ዝግጁ ናችሁ?
ተማሪዎች እስቲ አብረን ከታች ወደ ላይ እንደተማራችሁት ሁለቱን ሳጥን አንድ ላይ ስንደምር ውጤቱ ከላይ ያለውን አንዱን ሳጥን ይሆናል።
ይህ ማለት
የመጀመሪያ ሳጥን ሆሄ 1000 ውስጥ የሺ ቤት 1 ነው።(በቀስት 1000 ማመልከት)
ሁለተኛው ሳጥን ውስጥ 2000 የሺ ቤት ሆሄ 2 ነው።(በቀስት 2000 ማመልከት)
አሁን ደግሞ ልጆች ሁለቱን የሺ ቤቶች አንድ ላይ እንደምራለን 1 + 2 = 3 ይሆናል ማለት ነው።
በመቀጠል በቀኝ በኩል ያሉትን ሶስት ዜሮዎች እንጨምራለን ማለት ነው።(በቀስት ያሉትን 0 መደመር)
ስለዚህ የመጀመሪያ ሳጥን 3000 ይሆናል ማለት ነው። በመቀጠል ተማሪዎች 2000 እና 5000 አንድ ላይ እንደምራለን ማለት ነው። 2000 የሺ ቤት 2 የ 500 የሺ ቤት 5 ነው።(በቀስት የ 2000 እና 5000 ማመልከት)
ሁለቱን አንድ ላይ ስንደምር( 2 + 5 = 7 ይሆናል ማለት ነው።
በመቀጠል በቀኝ በኩል ያሉትን ሶስት ዜሮዎች እንጨምራለን።(በቀስት ያሉትን 0 መደመር) 7000 ይሆናል።
ተማሪዎች ስለዚህ የመለሳቹት መልስ ትክክል ነው ማለት ነው። ተማሪዎች አሁን ደግሞ ባለሶስት ሆሄ ቁጥሮችን ከባለ ሶስት ሆሄ ቁጥሮች ጋር መደመር እንማራለን ።
ባለ ሶስት ሆሄ ሙሉ ቁጥሮችን ከባለ ሶስት ሆሄ ሙሉ ቁጥሮች ጋር ቁልቁል መደመር የተማራቹትን ታስታውሳላችሁ አይደል?
ካስታወሳቹ ካታች ያሉትን ቁጥሮች ቁልቁል ደምሩ።
ምሳሌ ቁጥር 1 ሀ) 380 +15
ተማሪዎች አስተውሉ ከአንድ ቤት በመጀመር ሆሄዎችን መደመር።በአለኝታ የሚደመሩ ከሆነ አለኝ የሚለውን ቁጥር ከሚቀጥለው ትልቁ ቁጥር ቤት ሆሄዎች ጋር መደመር እንዳለባችሁ።
በዚህ መሰረት እስቲ ምሳሌ አንደን ቁልቁል እንደምር 380 +15
(0 + 5 =5 ) ተማሪዎች 5 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው።
380 +15 5 አሁን ደግሞ (8 + 1 = 9) ተማሪዎች 9 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው።
380 +15 95 በመጨረሻም (3 ብቻዋን ስላለች አሌንታም ስለሌላት ከማንም ጋር ሳትደምር 3 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው። 380 +15 395 ምሳሌ ቁጥር 2
ለ) 420
+16 (0 + 6 = 6 ) እንደተማራቹት ማንኛውም ቁጥር ከ 0 ጋር ስንደምር እራሱ ቁጥሩ ይሆናል ስለዚህ ተማሪዎች 6 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው
420
+16
6
(2+ 1 = 3 )ተማሪዎች 3 ብላን እንጽፋለን ማለት ነው
420
+16
36
በመጨረሻም (4 ብቻዋን ስላለች አሌንታም ስለሌላት ከማንም ጋር ሳትደምር 4 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው።
420
+16
436 ተማሪዎች አሁን ደግሞ እስካሁን የተማራችሁትን ጥያቄ ልጠይቃችሁ
ሐ) 303
+11 ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት?በጣም ጥሩ!
414 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኃል ማለት ነው።
ተማሪዎች ይህንን ለማረጋገጥ እስቲ አብረን እንስራ
እንደ ተማራችሁት ከአንድ ቤት በመጀመር ሆሄዎችን ከኃላ ወደ ፊት እንደምራለን።
ስለዚህ ተማሪዎች በመጀመሪያ ( 3 + 1 = 4) ተማሪዎች 4 ብላን እንጽፋለን ማለት ነው
በመቀጠል (0 + 1= 1 )ተማሪዎች እንደተማራቹት ማንኛውም ቁጥር ከዜሮ ጋር ሲደመር እራሱ ቁጥሩ ይሆናል ስለዚህ 1 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው
በመጨረሻም 3 ብቻዋን ስላለች አሌንታም ስለሌላት ከማንም ጋር ሳትደምር 3 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው።
ስለዚህ ተማሪዎች እዚህ ጋር 303
+11
314 መ) 314 +20 ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት?በጣም ጥሩ!
434 ብለችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኃል ማለት ነው።
ተማሪዎች ይህንን ለማረጋገጥ እስቲ አብረን እንስራ
እንደ ተማራችሁት ከአንድቤትበመጀመርሆሄዎችን ከኃላ ወደ ፊት እንደምራለን።
ስለዚህ ተማሪዎች በመጀመሪያ ( 4 + 0 = 4) ተማሪዎች 4 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው
በመቀጠል (1 + 2 = 3 )ተማሪዎች እንደተማራቹት ማንኛውም ቁጥር ከአንድ ጋር ሲደመር እራሱ ቁጥሩ ይሆናል ስለዚህ 3 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው
በመጨረሻም 3 ብቻዋን ስላለች አሌንታም ስለሌላት ከማንም ጋር ሳትደምር 3 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው።
ስለዚህ ተማሪዎች እዚህ ጋር 314 +20
334 ሠ) 240 +30
ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት?በጣም ጥሩ ተማሪዎች 270 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኃል ማለት ነው።
ተማሪዎች ይህንን ለማረጋገጥ እስቲ አብረን እንስራ
እንደ ተማራቹት ከአንድ ቤት በመጀመር ሆሄዎችን ከኃላ ወደ ፊት እንደምራለን።
ስለዚህ ተማሪዎች በመጀመሪያ ( 0 + 0 = 0) በመቀጠል (4 + 3 = 7 )
በመጨረሻም 2 ብቻዋን ስላለች አሌንታም ስለሌላት ከማንም ጋር ሳትደምር 2 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው።
ስለዚህ ተማሪዎች እዚህ ጋር 240
+30
270 አሁን ደግሞ ባለ ሶስት ሆሄ ቁጥሮችን ከባ ለአራት ሆሄ ቁጥሮች ጋር መደመር እንማራለን።
ባለ ሶስት ሆሄ ሙሉ ቁጥሮችን ከባለ አራት ሆሄ ሙሉ ቁጥሮች ጋር መደመር በተመሳሳይ መንገድ የሰራል። ዝግጁ ናችሁ ልጆች?
• ከአንድ ቤት በመጀመር ሆሄዎችን መደመር። • በአለኝታ የሚደመሩ ከሆነ አለኝ የሚለውን ቁጥር ከሚቀጥለው ትልቁ ቁጥር ቤት ሆሄዎች ጋር መደመር አለብን ማለት ነው። ለምሳሌ 1
ሀ. 3456
+123
ተማሪዎች በመጀመሪያ እንደተማሩችሁት ከአንድ ቤት መደመር እንጀምራለን ማለት ነው(6 + 3 = 9 )ተማሪዎች 9 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው 3456 +123 9
በመቀጠል (5 + 2 = 7) ተማሪዎች 7 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው 3456
+123 79
ከዛም (4 + 1 = 5 ) ተማሪዎች 5 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው 3456
+123 579
በመጨረሻም (3) ብቻዋን ስላለች አሌንታም ስለሌላት ከማንም ጋር ሳትደምር 3 ብለን እንጽፋለን ማለት ነው።
ስለዚህ ተማሪዎች እዚህ ጋር 3456 +123 3579 1) ተማሪዎች እስቲ አሁን ደግሞ ከታች ያሉትን ቁጥሮች ወደ ጎን እንደምር ዝግጁ ናችሁ?
ሀ) 4320+201 = 4300 + 20 + 200+ 1 (ተማሪዎች ይህ ማለት 4320 ዜሮ የአንድ ቤት ነው ፣ 2 የመቶ ቤት3 የሺ ቤት ስለዚህ የሺ ቤት ይሆናል 4300 እንናደርጋለን። ከዛም 201 ደግሞ የመቶ ቤት ስለሆነ 200 እንላለን ከዛም የቀሩትን ቁጥሮች 20 እና 1 በዚህ መልኩ እንፅፋለን ማለት ነው። = 4300 + 200 + 20 + 1
ከዛም 4300 እና 200 አንድ ላይ እንደምራለን ማለት ነው። 20 እና 1 ንም እንደዛው አንድ ላይ እንደምራለን። = 4500 + 21
በመጨረሻም 4500 እና 21 አንድ ላይ ስንደምር ደግሞ 4521 ይሆናል ማለት ነው። = 4521 ለ) 5723+112= 5700 + 20 + 3 + 100 + 10 + 2 (ተማሪዎች ይህ ማለት 5723 ሶስት የአንድ ቤት ነው ፣ 2 የመቶ ቤት፣ 7 የሺ ቤ ስለዚህ የሺ ቤት ይሆናል 5700 እንናደርጋለን። ከዛም 112 ደግሞ የመቶ ቤት ስለሆነ 100 እንላለን ከዛም የቀሩትን ቁጥሮች 20 ፣ 10 ፣ 3 ፣ 2 በዚህ መልኩ እንፅፋለን ማለት ነው። =5700 + 100 + 20 + 10 + 3 + 2
ከዛም 5700 እና 100 አንድ ላይ እንደምራለን ማለት ነው። 20 እና 10ን ከዛም 3 እና 2 ንም እንዛው አንድ ላይ እንደምራለን። = 5800 + 30 + 5
በመጨራሻም 5800 እና 30 እና 5 አንድ ላይ ስንደምር ደግሞ 5835 ይሆናል ማለት ነው። = 5835 2) ተማሪዎች አሁን ደግሞ የሚከተሉትን ቁጥሮች ቁልቁል ደምሩ።
ሀ) 3214 +123
ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት?በጣም ጥሩ!
3337 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኃል ማለት ነው። ለ) 6110 +321
ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኃል ማለት ነው።
6431 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኃል ማለት ነው። ሐ) 4120
+111
ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኃል ማለት ነው።
4231 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኃል ማለት ነው።
አሁን ደግሞ ድምራቸው እስከ 10,000 የሚደርሱ ባለአራት ሆሄ ቁጥሮችን ከባለ አራት ቁጥሮች ጋር መደመር እንማራለን።
ተማሪዎች አስታዉሱ!!
• ባለ አራት ሆሄ ሙሉ ቁጥሮችን ከባለ አራት ሆሄ ሙሉ ቁጥሮች ጋር ያለአለኝ ስትደምሩ ቁጥሮችን በቤት በቤታቸው መደመር ተገቢ ነው። በአለኝታ የሚደመሩ ከሆነ ደግሞ መጀመሪያ በአንድ ቤት ያሉትን ሆሄዎች መደመር ቀጥሎ በ10 ቤት፣ በ100 ቤት እና በ1000 ቤት ያሉ ሆሄዎች ይደመራሉ።
በየ ደረጃው አለኝ የምንለውን በሚቀጥለው ትልቁ ቁጥር ቤት ካሉት ሆሄዎች ጋር መደመር ምሳሌ ቁጥር 1
ሀ) 4321 +1264
መፍትሄ፡መጀመሪያ ቁጥሮችን ቤታቸውን ጠብቆ ቁልቁል መደመር ቀጥሎ በየ ብቤታቸው ሆሄዎችህ መደመር።ስለዚህ ተማሪዎች ይህ ማለት መደመር ምንጀምረው ከአንድ ቤት ነው (1 + 4 = 5) ቀጥለን ደግሞ የአስር ቤት (2 + 6 = 8) ከካም የመቶ ቤት እንደምራለን (3+ 2 = 5) በመጨረሻም ( 4 + 1 = 5) ተማሪዎች አሁን ደምርን ያገኘነውን ቁጥሮች በየቤታቸው እናስቀምጣለን ማለት ነው ። ስለዚህ 4321 +1264 5585
ምሳሌ ቁጥር 2
ለ) 2146 +1124
ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት?ጎበዞች!
3270 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኃል ማለት ነው።
በአሌንታ ስለሚደመር 6 + 4 = 10 ስለዚህ ተማሪዎች 0ን ጽፈን 1ን ወደ ሚቀጥለው ቁጥር ጋር እንደምራለን። ይህም ማለት 1 +4 = 5 ከዛም 5 ላይ 2ን እንድምራለን 5+2 = 7 ይሆናል ማለት ነው።
ተማሪዎች አሁን የቀሩትን ሆሂዎች እንደምር (1 + 1 = 2) እና ( 2 + 1 = 3) ስለዚህ ተማሪዎች 3270 ይሆናል ማለት ነው። ሐ) 3611 +1101
ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት?በጣም ጥሩ ተማሪዎች 4712 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኃል ማለት ነው። መ) 1234 +5678
ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት?በጣም ጥሩ ተማሪዎች 6912 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኃል ማለት ነው። ሠ) 4329 +2018
ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት?በጣም ጥሩ ተማሪዎች 6347 ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኃል ማለት ነው።
መፍትሄ፡መጀመሪያ ቁጥሮችን ቤታቸውን ጠብቆ ቁልቁል መደመር ቀጥሎ በየ ብቤታቸው ሆሄዎችህ መደመር። ተማሪዎች አሁን ደግሞ የቃላትፕሮብሌሞች እንፈታለን።
ተማዎች የቃላት ፕሮብሌሞችን ለመፍታት ወይም መፍትሄ ለማግኘት የሚከተሉትን የአሰራር ደረጃዎች መከተል ይገባል።
1ኛ፡ፕሮብሌሙን ደጋግሞ አንብቦ መረዳት
2ኛ፡የተሰጡትንና የሚፈለጉትን መለየት
3ኛ፡የሚፈለገውን ሰርቶ ማግኘትና መልሱን ማረጋገጥ
ምሳሌ ቁጥር 1
1. አቶ አበበ ሁለት ልጆቹን የተለያየ ትምህርት ቤት ያስተምራል ለመጀመሪያው ልጅ ከበደ በወር 3450 ብር የትምህርት ቤት ክፍያ ይከፍላል። ለሁለተኛው ልጅ ታደለች በወር 3750 ብር የትምህርት ቤት ክፍያ ይከፍላል የሁለቱን የትምህርት ቤት ክፍያ በወር ስንት ነው?
ተመሪዎች ጥያቄዎች ሞከራችሁት ?በጣም ጥሩ ተማሪዎች !
7200 ብር ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልውሳችኃል ማለት ነው።
ተማሪዎች ይህን ለማረጋገጥ እስቲ አብረን እንስራ።
ለከበደ በወር የትምርት ቤት ክፍያ 3450 ብር ለታደለች ደግሞ የትምህት ቤት ክፍያ 3750 ብር
አቶ አበበ በወር የሚከፍለውን ለማግኘት የሁለቱንም ልጆች ክፍያ አንድ ላይ ቁልቁል እንደምራለን ማለት ነው። 3450
+ 3750
ተማሪዎች እስቲ አብረን እንደምር
(0 + 0 = 0) ተማሪዎች 0 ብለን እንሞላለን (5 + 5 = 10) ስለሆን 0ን ፅፈን የቀረዉን 1 ደግሞ አሌንታ አለን ማለት ነው።
(4 + 7 = 11) ከዛ 1 አሌንታ የነበረንን እንደምራለን ማለት ነው ስለዚህ 11 + 1 = 12(አሁንም 2 ፅፈን 1ን አሌንታ ይኖረናል )
(3 + 3 = 6) አንድ አሌንታ የቀረንን 6 + 1 = 7 ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ ልጆች እዚህ ጋር 3450
+ 3750
72 00